ሶስት የበረራ አስተናጋጆቹ በቅርቡ የኮሮናቫይረስ እንዳለባቸወ ያስታወቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለበረራ ሰራተኞቹ በለጠፈው ማስታወቂያ COVID 19 ምርመራ ማድረግ ለሚፈልጉ በጊቢ ውስጥ ያለውን የሚዲካል ቲሙን በማግኘት ምርመራ ማድረግ እንደሚችሉ አስታውቋል።

ከበረራ በኋላ ወይንም ከዛ ውጭ የበረራ አስተናጋጆቹና ፓይለቶቹ የአየር መንገድ ግቢ ውስጥ በየትኛውም ሰዓት ምርመራ ማድረግ እንደሚችሉ አሳውቋል
ሆኖም ግን ” ፈጣን የኮቪዲ19″ ምርመራ ማለቱ በተወሰኑ የአየር መንገዱ ሰራተኞች በኩል ትችት አስከትሎበታል።
ሰሙ እንዳይገለፅ ያልፈለገ የአየር መንገዱ ሰራተኛ ” ማስታወቂያው ከተለጠፈ በኋላ ሰዎች እየተመረመሩ ነፃ ነኝ ብለው ሲደሰቱ እያየን ነው ።የኮሮና ምርመረ ውጤት ቢያንስ 24 ሰዓት ይፈጃል ። ይሄ ግን እየተደረ አይደለም “ብሏል ።
ፊደል ፖስት የአየር መንገዱን የህዝብ ግንኙነት ክፍል በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የጠየቀ ሲሆን ” ነገሮች ሁላ ጤና ሚኒስትር መመርያን ጠብቆ ነው እየተከናወነ ያለው ።በተጀመረው ምርመራ ላይ ለሚዲያ በቅርቡ መግለጫ እንሰጣለን ” የሚል ምላሸ አግኝቷል።
ፊደል ፖስት ጤና ሚኒስትርን የጠየቀ ሲሆን መልስ ለማግኘትም እየተጠባበቀ ይገኛል።