” ኮሮና ቫይረስ ለካስ በወዳጅ መቀበርም ክብር ነበር አስብሎኛል “ዶ/ር ወዳጄነህ


በበድር ፋውንዴሽን አማካኝነት ዛሬ በአዲስ አበባ በሞናርክ ሆቴል ” ሳይዛመት በህብረት ” በሚል በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሰርጭትን ለመግታት ላይ ስድስት ሰዎች ብቻ በተሳተፉበት የፓናል ውይይት ላይ የተገኙት ዶ/ር ወዳጄነህ መሃረነ እንዳለት ኮሮና ቫይረስ አለምን ማህበራዊ እሴቷን እያሳጣት ነው ብለዋል ።
” አንዲት ጣልያን ሀገር ያለች የማውቃት ወዳጄ ባሏ በኮሮና ቫይረስ ሞቶባት ለመቅበር ሰባት ቀን ነው ወረፋ የጠበቀችው ። ይሄ ያማል ። ቶሎ በሰው ለመቀበርም ለካ ክብር ነው እንድል አስችሎኛል።”

“የቫይረሱ ወጀብ ወደ እኛ መጥቷል ።በስፋት ሳይሰራጭ የሀኪምን ምክር በመስማት ፣እርስ በእረስ በመደጋገፍ ፣በመፀለይ ቫይረሱን ስርጭት ማስቆም” ይገባናል ብለዋል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *