የኢትዮጵያ አየር መንገድ የፕሌን አብራሪዎች ማህበርን ለበርካታ አመት በፕሬዝዳንትነት ያገለገለውን ካፒቴን የሽዋስ ፋንታሁን ዛሬ የአየር መንገዱ ካፒቴኖች “ለጥቅማችንና ለመብታችንን እንድንታገል እንዲሁም የምንወደው አየርመንገዳችን በቅንነትና በትጋት እንድናገለግል ላደረግከው አስተዋፅኦ” ምስጋና ይገባካል በማለት የ1.6ሚልዮን ብር ስጦታ አበርክተውለታል።ካፒቴን የሺዋስ ለፊደል ፓስት እንደተናገረው ” ጓደኞቼ ላበረከቱልኝ ስጦታ አመሰግናለው ።አሁን እንግዲ የኢትዮጵያ አየርመንገድ መሰረታዊ ሰራተኞች ማህበርን አየመራው እገኛለው ።ማህበሩ ለሰራተኞች መብት ለማስከበር ግዴታቸውንም በይበልጥ ለማሳወቅ ረገድ ብዙ ነገር ለመስራት አልሞ የተነሳ ነው። ብዙ እንቅፋቶች ቢኖሩበትም በተቻለኝ አቅም ከማህበሩ አባላት ጋር በመቀናጀትና በመተባበር የአቅሜን እሰራለው ” ሲል ተናግሯል።