የከተማው ማህበረሰብ ከአርሶ አደሩ ጋር በጋራ የእርሻ ምርት የሚያመርቱበት ዳርዜማ የተባለ አክስዪን ማህበር ተቋቋመ

አርሶ አደሩ ቢያንስ በአመት ሶስትጊዜ እንዲያመርትለማድረግና በአነስተኛ መሬትየተቀናጀ( mechanized) የእርሻ ስራን በማላመድ ውጤታማ የሚያድርግ መሆኑም ተመላክቷል።
በአምስት ሺሕ ሄክታር 3800 አርሶ አደሮችን በማሳተፍ ስራው ይጀምራል የተባለ ሲሆን በተለያየየ ውሃ ምንጭ ማለትምበኩሬ፡ በወንዝ ፡በከርሰምድር፡ ሊለሙ የሚችሉ በየትኛዉም የሃገራችን አካባቢ እሰከ 400,000 ሔክታር ላይ አገልግሎት ለመስጠት ማቀዱን ድርጅቱ አስታውቋል።
የአክሲዮን ማሕበሩ መስራች አቶ ዘላለም እሸቱ የአርሶ አድሩን የሰብል አመራረት ሳይንሳዊ እንዲሆን በማድረግ ምርት እና ምርታማነትን መጨመር ግብ በማድረግ ስራ መጅመሩን ተናግረዋል።
በዳርዜማ የግብርና ግብአት አቅርቦት ሰንሰለት አማካኝነት አርሶ አደሩ በአንድ ሄክታር መሬት ላይ እስከ 90 ኩንታል ምርት እንደሚያስገኝለት ባደረግነው ቅድመ ጥናት ተረድተናል የሚሉት አቶ ዘላለም አምራቹ ምርቱን ወደ ገበያ ሲያወጣ ከአንድ ግዜ ምርቱ ከ3 መቶ ሺህ ብር በላይ ማግኘት ያስችለዋል ሲሉም አብራርተዋል።
ለአርሶ አደሩ የሚሰጠውን አገልግሎት በተመለከተ ሲገልጹም ከምር፟ጥ ዘር ጀምሮ ዘመናዊ የእርሻ ስራ ቴክኖሎጂዎች አቅርቦት እንደሚያጠቃልል አመላክተው ከዚህ ባሻገርም የተዘራው ዘር ምርት ለመስጠት የሚያስፈልገው ግዜ መነሻ በማድረግ የግብርና ባለሞያዎችን ተመመድበው የምርት ትርፋማነት ላይ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
በየ20 ሄክታር መሬት አንድ የግብርና ባለሞያ በሙሉ ግዜ የሚመደብ ሲሆን አጠቃላይ ሂደቱን በማማከር ውጤታማነቱን እናረጋግጣለንም ብለዋል።


ከዚህ ቀደም መንግስት የአርሶ አደሩን ትርፋማነት ለመጨመር ምርጥ ዘር እና ማዳበሪያ ከማቅረብ ጀምሮ የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ይታወሳል።
በሃገሪቱ የምርት እጥረት መኖሩን አጽንኦት የሚሰጡት አቶ ዘላለም ዳርዜማ በዚህ ዘርፍ ትኩረት አድርጎ በመስራት በሃገሪቱ የመጀመሪያው መሆኑን አስምረውበታል።
የአገልግሎትክፍያዉንበተመለከተሲያብራሩም“ አንድሔክታርያለዉአርሶአደርበትራክተርልረስቢልበአማካኝ8000 ሸህብርዎጭአለበት ፤ይህአርሶአደርበመሬቱላይ45ኩንታል ስንዴአገኝብንልለማሳጨጃእናለመፈልፈያለኩንታል150ብርያዎጣል፡አሁንባለዉተጨባጭመረጃይህምበድምሩ6750ብርሲዎጣበአጠቃላይ14,750ብር እንዲከፍሉይሆናሉ ፤ይህለእርሻእናለመፈልፈያየሚዎጡትገንዘብብቻነው፤የምርጥዘርእናየማዳበሪያእንዲሁምየግብርናባለሞያሳይጨምርነው። በዳርዜማአማካኝነትግባት ፡የባለሙያአገልግሎት ፡የእርሻአገልግሎት፡የአጨዳእናመዉቂያአገልግሎትቀርቦለትበተመሳሳይ 1 ሔክታርመሬት18000 ሸህብርብቻይሆናል፡፡ ከአንድሄክታርመሬትላይምእስከ 90 ኩንታልስንዴበማስገኘት316 ሺህብርማግኘትይችላል”  ፡፡ይህበአንድግዜምርትሲሆንአመቱንሙሉእስከ 3 ግዜድረስምርትበማምረትትርፋማነቱንምውጤታማነቱንምመጨመርይቻላልነውያሉት።
ዳርዜማን የተለየ ከሚያደርጉት ጉዳዮች ውስጥ በዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂዎችና በግብርና ባለሞያዎች ከአርሶ አደሩ ጥርት ጋር ተዳምረው የምርት ብክነትን ሙሉ በሙሉ የሚያስቀር መሆኑና አርሶ አደሩ በሰው ሰራሽ ሆነ በተፈጥሯዊ ምክንያቶች ኪሳራ ቢያጋጥመው ኪሳራውን ዳርዜማ የሚወስድ መሆኑ ነው። ይህም የአርሶ አደሩ ውጤታማነት ተቀዳሚ ትኩረቱ በመሆኑ ነው ብለዋል።
እንደ ሙከራ በሚል በአምስት ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ስራው ሲጀመር በትንሹ 450 ሺሕ ኩንታል ምርት የሚገኝ ሲሆን ይህ ወደ ገንዘብ ሲቀየር 1 ነጥብ 65 ቢሊየን ብር ማመንጨት ያስችላል ።
ሙሉ በሙሉ ስራው በ 4 መቶ ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የማዳረስ እቅድ የተያዘ ሲሆን ይህም በትርሊየን ብር የሚጠጋ ሃብትን የሚያንቀሳቅስ ይሆናል።
ይህንን አክሲዮን ማህበር በተለይ ከግብራ ስራ የራቀ የሚመስለው ከተሜ አክሲዮን በመግዛት ባለቤት እንዲሆን ጥሪ ቀርቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *