አረንጓዴ እጆች” በሚል መጠሪያ ፕሮግራም በ ቢ ጂ አይ ኢትዮጵያ ሰራተኞች የችግኝ ተከላ ተካሄደ።

እንጦጦ ፓርክ ውስጥ ከጠቀሜታዊ ፋይዳ አንፃር ሀገር በቀል ብቻ የሆኑ ችግኞች ተተክለዋል። ሰራተኞቹ በአረንጓዴ አሻራ ላይ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ዘንድሮም የራሳቸውን አሻራ ሲያሳርፉ አምና የተከሏቸውንም ችግኞች ጎብኝተዋል። በፕሮግራሙ ላይ ከተለያዩ ሚዲያ የመጡ ቁጥራቸው በርከት ያለ የሚዲያ ባለሙያዎችም በችግኝ ተከላ ፕሮግራሙ ላይ ተሳትፈዋል።

ከዚህም ባሻገር ቢ ጂ አይ ኢትዮጵያ መርካቶ አካባቢ በተነሳ የእሳት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ቤተሰቦች መልሶ ለማቋቋም በማህበራዊ ተሳትፎ የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት በማሰብ የ አንድ መቶ ሰባ ሁለት ሺህ ብር ድጋፍን አበርክቷል ለቤተሰቦች አበርክቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *