ሀያ ብር በማይሞላ የኤሌትሪክ ፍጆታ እስከ 500 ኪሎ ሜትር የሚጓዙት የግሪን ትራንስፖርት መኪኖች በአዲስ አበባ ጎዳናዎች እየተዋወቁ ነው
የተሳፋሪ መጫን አቅማቸው ከአምስት እሰከ 23 የሆኑት ትንንሽ አውቶሞቢሎችና ሚዲ ባሶች በኤሌትሪክ ባትሪ የሚሰሩ የግሪን ትራንስፖርት መኪናዎች ለከተማዋ ነዋሪዎች ለማቅረብ በነፃ ትራንስፖርት የማስተዋወቅ ስራ ተጀምሯል።

በስድስት መነሻ ቦታዎች ነፃ የትራንስፖርት ይሰጣል ተብሏል ።
ለአንድ ወር ያህል በነፃ ህብረተሰቡን ከቦታ ቦታ የሚያመላልሱ ሲሆኑ እነዚህ ሚዲባሶች አንድ ጊዜ በ 18 ብር ብቻ ባትሪያቸውን በኤሌክትሪክ የሚሞሉ ሲሆን 500 ኪሎሜትሮችን መጓዝም ይችላሉ። በከተማዋ አዲስ አበባ 40 የሚሆኑ ባትሪ የሚሞላባቸው የኤሌክትሪክ ማደያዎችን በተለያዩ ነዳጅ ማደያ ስፍራዎች ተገጥመዋል።