ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ እጣን በማጠን ፈጣሪዋ ኮሮና ቫይረስን ከአለም እንዲያጠፋ ተማፀነች




በቅዱስ ሲኖዶስ ትእዛዝ ዛሬጠዋት በአዲስ አበባና በሌሎች የሀገሪቱ ስፍራዎች ጠዋት ከደብራቸው ወደ መንገድ የወጡት ቄሶች ፣ዲያቆናትና ምእመናን ዘማሪያን እጣን በማጠን በአለም ላይ ከ13,000 በላይ ሞትና ከሩብ ሚልየን በላይ ሰው አልጋ ላይ የዋለውን የኮሮና ቫይረስን እንዲያጠፋ ተማፅነዋል። ምእመናንም እጣኑ በሰፈራቸው ሲያልፍ እያጀቡ ስርአቱን ታድመዋል።


ፊደል ፖስት ዘጋቢ ስርአቱን ለመታደመ ወልደ ነጎድጓድ ሐዋርያ ቅዱስ ዪሀንስ ቤ/ክ የተገኘ ሲሆን እጣኑ ከቤ/ክርስቲየን ሲወጣ በስፍራው የነበሩ የእምነቱ ተከታዮች እጣኑን በመታጠን ፈጣሪያቸውን የኮሮና ቫይረስን ከአለም እንዲያጠፋ ተማፅነዋል ። በአንዳንዱ ሰው ላይ እንባና ጭንቀት ይታይ ነበር ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *