አብነት አካዳሚ አክስዮን በመሸጥ ወደ ማህበረሰብ ት/ ቤት ሊቀየር ነው

      የዛሬ  12   በመምህር ቴድሮስ  ወርቅነህ  በ70 ተማሪዎች  በመዋዕለ ህፃናት    ብሪታኒክ አካዳሚ  በመባል የተከፈተው  ከዛም ወደ አብነት አካዳሚ በመባል ያደገው በአሁኑ ሰአት  ከ 900 በላይ እስከ ስምንተኛ ክፍል  የሚያስተምረው ት/ ቤት  200 ሚልየን ብር  ድረስ የሚያወጣ  አዲስ  የማህበረሰብ  ት/ ቤት  ለማስገንባት  ማቀዱን አሳውቋል።
በሶስት ሺ ካሬ ላይ  የሚያርፈው አዲሱ ት/ ቤት  የልዩ ፍላጎትና  እና  ከ ዘጠኝ እሰከ  12  ማስተማርያ ክፍሎች  ይኖሩታል ተብሏል።

አቶ ቴድሮስ  ትናንት ከአብነት ነዋሪዎች በብሔራዊ ቲያትር አዳራሽ  በነበረ ውይይት  ላይ እንደተናገሩት  ”  ት/ ቤት በግለሰብ  መያዝ አለበት ብዬ አላምንም ።   ከግሌ አውጥቼ   አክስስዮኖች በመሸጥ   ባለቤቱን ወደ ማህበረሰብ መቀየር እፈልጋለሁ ። ለዚህም እየሰራን  እንገኛለን ። መሬት መንግስትን መጠየቅ  ከአክስዮን በተጨማሪ  ለግንባታ  ሌላ  ገንዘብ ማፈላለጊያ  ዘዴዎችን እንፈልጋለን ” ብለዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *