ብዙ ስለሆነ አዲስ አበባ የተመላለሱበትን ጊዜ ቤቱ ይቁጠረው። አማረኛ አቀላጥፈው ባይናገሩም መግባባት በደንብ ይችላሉ ።እርጋታ ፣አርቆ አሳቢነት ፣በጨዋታና በስብሰባ መሀል የሚሰጡት ትንታኔ ከመፅሀፍት ጋር ጥልቅ የሆነ ቁርኝነት እንዳላቸው ያሳብቃል። አቶ መለስ ዜናዊ ከመሞታቸው አመት ቀድም ብሎ የተባበበሩት መንግስታት ከኢትዮጵያ ስምንት ቢልየን ዶላር ሸሽተዋል ሲል አዲስ አበባ የነበሩት ሀምዶክ ” እንዲህ አይነት ብር ሸሸ ሲባል ይዘገንናል።ከደሀ ህዝቦች ጉሮሮ እየተሰረቀ የሌቦችን ኪስ ማደልብ ተገቢ አይደለም ።ይሄ አይነቱን ተግባር አፍሪካ አጥብቃ ልትዋጋ ይገባል ” ብለው ነበር።
ካዛንችስ በሚገኘው የተባበበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኒሚ ኮሚሽን በምክትል ፀሀፊነት ከ2003 አስከ 2010 ዓ.ም መጀመርያ የሰሩት ሃምዶክ በኮትዲቫርና የአፍሪካ ልማት ባንክላይ በዚምባብዌ ደግሞ በአለም አቀፊ የሰራተኞች ድርጅት ውስጥ ከፍተኛ ሀላፊ በመሆን ሰርተዋል። በሱዳንም ከ40 አመት በፊት ለተወሰነ አመት የገንዘብና የኢኮኖሚ ሚኒስትር ውስጥ ተቀጥረው ሰርተዋል።
ከዛሬ 64 አመት በፊት አሁን ህዝቧ ሶስት ሚልየን ህዝብ ባላት በማእከላዊ ሱዳን ኮርዶፋን ግዛት የተወለዱት ሃምዶክ ወታደራዊ በሆነው አካዳሚ ትምህርት ቤት በሱዳን የተከታተሉ ሲሆን ከዛም በመቀጠል በግብፅና በጆርዳን ተምረዋል ።
በኢኮኖሚክስ የመጀመርያ ዲግሪያቸውን ከካርቱም ዩንቨርስቲ ሲያገኙ የማሰትሬት እና የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ከእንግሊዙ ማንቸስተር ዩንቨርስቲ አግኝተዋል።
የሁለት ልጆች አባት የሆኑ ሃምዶክ እንደሳቸው ኦኮኒሚስት ከሆነችው ሙና አብደላ ጋር ከ27 አመት በፊት ትዳር የመሰረቱ ሲሆን በሱዳን ሴቶችን የፈለጉትን መልበስ ፣በፈቀዱት መስክ መደራጀት እና መስራት የሚገድበውን ህግ ” አፋኝ፣ሰብአዊ መብትን የሚጋፋ እና ለአምባገነኖች የተመቸ “በማለት በተደጋጋሚ ኮንነው የነበረ ሲሆን ህጉ አምና ሲነሳ ሃምዶክ የሀገራቸውን ዜጎች እንኳን ደስ አላቹ ብለው ነበር።
በ2011 ነሀሴ ላይ ሱዳንን ለ30 አመት የገዙት ኦማር አልበሽር ከስልጣን መነሳት ተከትሎ ወደ ስልጣን የመጡት ሃምዶክ ዛሬ ካርቱም ላይ በተወረወረው ቦንብ ግድያ የተሞከረባቸው ሲሆን ” አልሞትኩም ።የጀመረነውን ለውጥ አጠናክረን እንቀጥላለን ” በማለት በቲዊተር ገፃቸው አስፍረዋል።
የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድም “በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ላይ ዛሬ የተቃጣውን የግድያ ሙከራ አወግዛለሁ። የሱዳን ሕዝብ ሰላሙን ለማስጠበቅ ከፍተኛ ዋጋ ከፍሎ የሚደነቅ ርምጃ ወስዷል። እንዲህ ያሉ ክሥተቶች የሱዳንን መረጋጋትና የለውጥ ጉዞ ሊያደናቅፉ አይገባም።” በማለት ጥቃቱን አውግዘዋል።
በሱዳን የጋሸበውን የኑሮ ውድነት ፣ ከፍተኛ፣ስራ አጥነትንና የሀገሪቱን ሰላም ለመመለስ እንደሚሰሩ ቃል የገቡ ሲሆን ሱዳንን አሜሪካ ከፃፈችባት “የሽብርተኛ ተባባሪ ሀገር ” የሚለውን ቃል ያሰርዛሉ ተብሎ ይጠበቃል።