በኮሮና ስጋት የወደቁት ባለሀብቶች የባንክ ብድር መክፈያቸው ለአንድ አመት እንዲራዘም ጠየቁ



በሀገሪቱ ያሉ የተለያዩ እንቨስተሮች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሰራተኞች እየቀነሱና ገቢያቸውም አየቀነሰ መሆኑን ለገንዘብ ሚኒስቴር ገልፀው በዚህ ሁኔታ ከባንክ የተበደሩትን ብር ውል በገቡት መሰረት መክፈል አንደማይችሉ ገልፀዋል።
ሚኒስቴር መስርያቤቱም የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ አይቶ ከመንግስትም ሆነ ከግል ባንክ የተበደሩትን ብድር ለአንድ አመት ሳይከፍሉ እንዲራዘምላቸውና ስራቸው እንዲያንሰራራም ተጨማሪ ብድር የሚያገኙበትን ሁኔታ ሚኔስትሩ እንዲያመቻችላቸው መጠየቃቸውን ለፊደል ፖስት ተናግረዋል ።


ከባለሀብቶቹ ውስጥ የሆቴል ፣የውጭ ንግድ እና የማምረቻ ፍብሪካ ያላቸው ባለሀብቶች ይገኙበታል።

ከሚኒስቴር መስርያ ቤቱም በጎ ምላሽ እንዳገኙም ገልፀዋል በጉዳዩ ላይ መንግስት በቅርቡ የደረሰበትን ውሳኔም ያሳውቃል ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *