ጋሞ በክልል እንጂ በክላስተር መደራጀትን አይፈልግም” ጋዴፓ

“ጋሞ በክልል እንጂ በክላስተር መደራጀትን  አይፈልግም”የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ጋዴፓ)

ክልሎች በአዲስ መልክ እየተዋቀሩ እና እየተደራጁ ያሉበትን አካሄድ በተመለከተ ፓርቲው ያለውን አቋም ለሚዲያ አካላት ዛሬ በአዲስ አበባ መግለጫ ሰጥቷል።

በ 2010 ዓ.ም ለ ደቡብ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አቅርቦት የነበረውን ክልል የመሆንን ጥያቄ ክልሉ በአግባቡ ሳይመልስላቸው እንደቀረ አብራርተው የተናገሩ ሲሆን  ጥያቄውንም ድጋሚ ለፌዴሬሽን ምክርቤት አቅርበው ምላሽ እየተጠባበቁ ባሉበት ሁኔታ ላይ ግልፅ ባልሆነ አሰራር እና ህገመንግስታዊ ባልሆነ ውሳኔ አሰጣጥ ክልል የመሆን ጥያቄያችን ውድቅ ተደርጓል ብለዋል። በክላስተር አደረጃጀት እንዲደራጁ የተደረገበትን አሰራር የጋሞ ህዝብ ላይ በደል እንደመፈፀም ነው ሲሉም ቅሬታቸውን ተናግረዋል።

የጋሞ መማክርትና የሽማግሌዎች ማህበርን ወክለው ንግግር ያቀረቡት አቶ ሰጢቃ ሲሜ አንዳሉት ” ጋሞ ሰፊ ህዝብ ነው። የራሱ ባህል እና ማንነት ያለው ህዝብ ነውና ከሌሎች የራሳቸው ባህልና ማንነት ካላቸው ህዝቦች ጋር ተጨፍልቆ ሊታይ አይገባውም።
በራሳችን ቋንቋ ነው ልንስተዳደር የምንሻው አዲሱ አደረጃጀት ደግሞ ይህንን አይፈቅድምና ክልል የመሆን ህገመንግስታዊ መብታችን ሊነፈግ አይገባም “ብለዋል።

በክላስተር ያለው አደረጃጀት ፍትሃዊ እድገትን ለከተሞች እንደማያመጣና የጋራ መተማመንንም እንደሚያጠፋ የ ሀዋሳ ከተማን ዋቢ አድርገው አስረድተዋል።

ከዚህ በመቀጠል መንግስት የህዝቡን ህገመንግስታዊ መብትና ጥያቄ እንዲመልስ  በንግግራቸው አስገንዝበዋል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *