የኢትዮጵያውያንና የውጭ ሀገራት ባለሀብቶች የሽርክና ንግድ ለ25,000 ዜጎች ስራ አስገኝቷል።ኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች የተሻለ ቴክኖሎጂ እና ገቢ ለማግኘት በማሰብ ከውጭ ሀገር ባለሀብቶች ጋር አየመሰረቱት ያለ የሽርክና ንግድ ከጊዜ ወደ ጊዜ አየጨመረ መምጣቱን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ።
የኮሚሽኑ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ መኮንን ሀይሉ ለፊደል ፓስት እንደተናገሩት በአማካኝ በአመት ከ70 አሰከ 80 የውጭ ሀገራትና የኢትዮጵያውያን የሽርክና ንግዶች አየተመሰረቱ መሆኑን ተናግረዋል።
በአሁኑ ሰአትም 16 ቢልየን ብር ካፒታል ያላቸው 182 የሽርክና ንግዶች በምርትና ፣በግብርና ፣በሆቴልና ሪዞርት ስራ ላይ ተሰማርተው ለ25,000 ዜጎች የስራ እድል ፈጥረዋል ብለዋል።
ከኢትዮጵያውያን ጋር ከሚሰሩት የውጭ ሀገር ባለሀብቶች ውስጥ የቻይና፣አሜሪካ እና የህንድ ባለሀብቶች የመጀመሪያዎችን ደረጃ ይዘዋል።
ወደ 380 የሚጠጉ የኢትዮጵያውያንና የውጭ ሀገራት የሽርክና ንግዶች ወደ ስራ ለመግባት ዝግጅት ላይ እንዳሉም አቶ መኮንን ገልፀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *