የዛሬ 12 በመምህር ቴድሮስ ወርቅነህ በ70 ተማሪዎች በመዋዕለ ህፃናት ብሪታኒክ አካዳሚ በመባል የተከፈተው ከዛም ወደ አብነት አካዳሚ በመባል ያደገው በአሁኑ ሰአት ከ 900 በላይ እስከ ስምንተኛ ክፍል የሚያስተምረው ት/ ቤት 200 ሚልየን ብር ድረስ የሚያወጣ አዲስ የማህበረሰብ ት/ ቤት ለማስገንባት ማቀዱን አሳውቋል።
በሶስት ሺ ካሬ ላይ የሚያርፈው አዲሱ ት/ ቤት የልዩ ፍላጎትና እና ከ ዘጠኝ እሰከ 12 ማስተማርያ ክፍሎች ይኖሩታል ተብሏል።

አቶ ቴድሮስ ትናንት ከአብነት ነዋሪዎች በብሔራዊ ቲያትር አዳራሽ በነበረ ውይይት ላይ እንደተናገሩት ” ት/ ቤት በግለሰብ መያዝ አለበት ብዬ አላምንም ። ከግሌ አውጥቼ አክስስዮኖች በመሸጥ ባለቤቱን ወደ ማህበረሰብ መቀየር እፈልጋለሁ ። ለዚህም እየሰራን እንገኛለን ። መሬት መንግስትን መጠየቅ ከአክስዮን በተጨማሪ ለግንባታ ሌላ ገንዘብ ማፈላለጊያ ዘዴዎችን እንፈልጋለን ” ብለዋል ።