ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ በአንጎላ በሀገሪቱ ልዩ የተባለ ዩንቨርስቲ ልትገነባ ነው



ላለፉት 22 አመት በአንጎላ የኖረችው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሳቤላ ዩኃንስ በዋና ከተማዋ ሉዋንዳ ላይ ከመንግስት በተሰጣት 12 ሄክታር ላይ ትልቅ የህክምና ዮንቨርስቲ ልትገነባ መሆኑን የሀገሪቱ በርካታ መገናኛ ብዙሀኖች ዘግበውታል።
የሚገነባው ዩንቨርስቲ ሁለት ሆስፒታሎች ጭምር ሲኖሩት እስከ3,000 ተማሪ አንዴ የማስተማር አቅም አለው ተብሏል። ሆስፒታሉ በአንጎላ ያለውን የሀኪሞች እጥረት ለመቅረፍ ያግዛልም ተብሏል።
” አንጎላን እንደ ሀገሬ ነው ማያት ። ይህች ሀገር ለእኔ ብዙ ሰጥታኛለች ።እኔ የሆነ ነገር ማድረግ ማበርከት እፈልጋለው ።እዚህ የተማረ ሰው ብዙ የለንም ።ብዙ የሙያ ነክ ስራዎች ከውጭ በመጡ ሰዎች ነው የሚሰራው ። የተማረ ሰው ብዙ ማፍራትና ሀገሪቷን ማሳደግ ስለምፈልግ ነው ይሄን የህክምና ዩንቨርስቲ የምገነባው ” በማለት ቲፒኤ ለተባለ የቴሌቭዥን ጣቢያ አስተያየቷን ገልፃለች።
ባለፈው አመት የአንጎላ ዜግነት የተሰጣት ሳቤላ በብሎኬት ማምርት ስራ ጀምራ አሁን ላይ ትልቅ የኮንስትራክሽን እቃ ማምረቻኩባንያ ሲኖራት በግንባታ ስራ ላይም ትሳተፋለች ።ከ400 በላይ ሰራተኞችም አሏት ።አንጎላውያንም “ማዳም ሳቢና” በማለት ይጠሯታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *