በጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ የጋራ መኖርያ ቤቶችን ለመገንባት ከሩብ ቢልየን ብር በላይ ቤት ገንቢዎች በባንክ ብር አስቀምጠዋል ተባለ።

1,050 ቤቶችንም ለመገንባት አራት ሳይቶች መመረጣቸውም ተገልፇል።

በቀጣዩ አምስት አመት አንድ መቶ ሺ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን የመሬት ባለ ንብርቶችን ከቤት ገንቢዎች ጋር በማጣመር ስራ የጀመረው ጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ እስከ አሁን ድረስ 723 የቤት ተመዝጋቢዎች ከ253 ሚልየን ብር በላይ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣በዳሽን፣በአዋሽ እና በኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ
ከ253 ሚልየን ብር በላይ ማስቀመጣቸውን ተነግሯል።

በጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ ዛሬ በኢሊሊ ኢንተርናሽናሽናል ሆቴል ባቀረበው ሪፖርት በቡልጋርያ ማዞርያ ፣በላንቻ ፣በጣሊያን ኢምባሲ አካባቢ እና በጎሮ ሳይት 1,050 ቤቶችን ለመገንባት የአርትቴክቸራል ዲዛየን ተጠናቆ የግንባታ ፍቃድ ለማውጣት ሂደት መሆኑን ተጠቁሟል።
ሌሎች ቤቶችንም ለመገንባት የቦታ መረጣ ላይ አንደሆነም ተገልፇል።
ጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ ይዞታዬን እጋራለሁ በጋራ እገነባለሁ ከተማዬን አለማለሁ በሚል መርህ ባለይዞታዎችን ከቤት ፈላጊዎች ጋር በማስተሳሰር የመኖሪያ ቤት ችግርን የሚቀርፍ ሞዴል ይዞ 30 ከመቶ ከቤት ፈላጊዎች 70 ከመቶ ከባንኮች በሚገኝ የፋይናንስ አቅርቦት ቤት የሚገነባበትን አሰራር ይዞ መምጣቱ ይታወቃል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *