በአዲስ አበባ በአደንዛዥ እፅ እና በአልኮል መጠጥ ከባድ ሱስ የሚያዘው የአርቲስትና የዘፋኞች ቁጥር መጨመር አሳሳቢ ሆኗል
በአዲስ አበባ በሲጃራ፣ በጫት ፣በአልኮል መጠጥ ፣ ሺሻ አልፎ አልፎም አደንዛዥ ዕፅ ከባድ ሱስ የተያዙ ዘፋኞችና አርቲስቶች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ፊደል ፖስት ከዘፋኞችና አርቲስቶች ቅርበት ካላቸው ሰዎች የደረሰው መረጃ ያሳያል።
በከባድ ሱስ ከተያዙት መሀል በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነት ያላቸው ዘፋኞች ፣ ቲያትርና ፊልም ሰሪዎች ፣ዳይሬክተሮች ፣ ገጣሚዎችና ደራሲዎች የሚገኙበት ሲሆን ይሄም በጤናቸው ፣በትዳርና በማህበራዊ ሕይወታቸው ላይ እክል አየፈጠረባቸው መሆኑን ለፊደል ፖስት የደረሰው መረጃ ያሳያል።
በተጨማሪም በቲክ ቶክ እና በማህበራዊ ሚዲያ ከሚታወቁ ግለሰቦች መሀልም በአከባድ የአልኮል የመጠጥና የአደንዛዥ ዕፅ ሱስ የተዘፈቁ አሉም ተብሏል።