የአቡዳቢው አልጋ ወራሽ ቢን ዛይድ ለጋውን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርን አብይ አህመድን 3 ቢልየን ዶላር ኢንቨስትመንት ድጋፍ ሊሰጠው ቃል መግባቱ የአመት ከስድስት ወር ትዝታ ሲሆን ቃል ከተገባው ውስጥ አንድ ቢልየን ዶላሩ የውጭ ምንዛሬን ለመቅረፍ ሲባል ብሔራዊ ባንክ ገብቶ ጥቅም ላይ ውሏል። 4,000 አፓርትመንት ቤት የሚይዘው የላጋር ኤግል ሂል የአቡዳቢ ባለሀብቶች ፕሮጀክት ኢትዮጵያን የመፈለግ አንድ ማሳይ ነው ። የዪናይትድ አረብ ኢሜሬትሷ ዋና ከተማ አቡዳቢ 100 ሚልየን ዶላር ለወጣቶች ስራ ፈጠራ ለመስጠት ቃል ገብታለች ። ኳታር ለኩላሊት እጥበት ህክምና ማእከል ለመገንባት 47 ሚልየን ዶላር ትለግሳለች ተብሎ እየተጠበቀ ነው ።በኢትዮጵያ በቤት ግንባታ እና በፋይናንስ እና በማኑፍክቸሪንግ ላይ ለመሰማራት የንግድ ልዑኳኗን አልፎ አልፎም ቢሆን እየላከች ነው ። በአሁን ሰአት 3 የኳታር ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ስራ ላይ ናቸው።የቢን ሳልማኗ የኳታር ተፃራሪ ሳዑዲ በመጠኑ ከፍተኛ ነው የተባለላትን ለኢትዮጵያ 65 ሚልየን ዶላር ለጤናና ለንፅህና ሰጥታለች። ከሞጣ ደብረ ማርቆስ የሚገነባውን 117 ኪሎ ሜትር ለመገንባት እንዲያስችል 75 ሚልየን ዶላር ደግፋለች ።በአጠቃላይ ሳዑዲ አሁን በግብርናና በማኑፋክቸሪንግ ኢትዮጵያ ውስጥ 20 ፕሮጀክቶች አሏት ።
እንደ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በአሁኑ ሰአት የአረብ ሀገራት ስራ ላይ ያለ ኢንቨስትመንት ቁጥር 56 ደርሷል ።ከአራት አመት በፊት ከ 16 አይበልጥም ።ስራ ላይ ላይ ያሉት እነዚህ ፕሪጀክቶች ስራቸውን ሲጀምሩ ካፒታላቸው አንድ ቢልየን ብር ነበር ።አሁን ሁለት ወይም ሶስት እጥፍ ያድጋል ተብሎ ይታመናል ።ሳኡዲ፣ኳታር ፣የመን እና ሊባኖስን ጨምሮ በአማካኝ በአመት ወደ 35 የአረብ ሀገራት ፕሮጀክቶች ወደ ኢትዮጵያ እየመጡ ነው ። የመን 22 ሊባኖስ ደግሞ 10 ስራ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች ኢትዮጵያ ውስጥ አላቸው ። በአጠቃላይ ወደ 131 የአረብ ሀገራት ፕሮጀክቶች በኢትዮጵያበማኑፍክቸሪንግ ፣በግብርና ፣በግንባታ፣በሪል እስቴት እና ማሽነሪ ኪራይ ላይ ስራ ለመጀመር መስመር ላይ ናቸው ።